Announcement በልደታ ክ/ከተማ በ24/7 የስራ ባህል የተገነቡ የቅዱስ ጊዮርጊስና የፍሬ ህይወት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

በልደታ ክ/ከተማ በ24/7 የስራ ባህል የተገነቡ የቅዱስ ጊዮርጊስና የፍሬ ህይወት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

25th May, 2026

ት/ቤቶቹ በተለወጠ የስራ ባህል 24/7 በመስራት በ4 ወራት ውስጥ ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል።ከዚህ በፊት ተማሪዎች ለመማር ምቹ ባልሆነ አካባቢ ውስጥ ሲማሩ ቆይተው ለረጅም ጊዜ በማህበረሰቡና በመምህራን ዘንድ ቅሬታ ሲቀርብ ነበር።የለውጡ መንግስት ችግሩን በአጭር ጊዜ በመረዳት ደረጃውን የጠበቀ፣ ለመማርና ለማስተማር ምቹ የሆነ ዘመናዊ ት/ቤት ገንብቶ ለተጠቃሚዎች አስረክቧል።“በህፃናት ላይ መስራት የነገን ሀገር መገንባት ነው” በሚል መርህ የሚመራው የለውጡ መንግስት ትውልድን የሚቀርፁ ስራዎችን በትኩረት እየሰራ ሲሆን በትምህርት ዘርፍም ተጨባጭ ውጤቶችን አምጥቷል።ልደታ ክ/ከተማ በቀጣይም ለህፃናት የተሻለ የመማሪያ አካባቢ በመፍጠር ትውልድን የመገንባት ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል።

.

Copyright © All rights reserved.