(ነሀሴ 11/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ በመስከረም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተከናወኑ የሚገኙ የከተማ ግብርና ስራዎች ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የተማሩትን በተግባር እንዲያዩና ክህሎታቸዉን እንዳዳብሩ ከፍተኛ እገዛ በማድረግ ላይ መሆኑ ተገልጻል፡፡
በትምህርት ቤቱ ውስጥ ባሉ ክፍት ቦታዎች የተለያዩ የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ፣ እፅዋትን በማልማት እንዲሁም የበግና የዶሮ እርባታ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
በት/ቤቱ እየተከናወነ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት ስራ ተማሪዎችን ፣ መምህራንን ፣ የተቋሙን ሰራተኞችና አመራሮች ተጠቃሚ ከማድረጉ ባለፈ በአከባቢው ለሚገኙ ገበያዎች ምርቶችን በማቅረብ የኑሮ ውድነት እንዲቀንስና የገበያ መረጋጋት እንዲፈጠር የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አቶ ጌትዩ ምንዳ የመስከረም አጠቃለይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕስ መምህር ገልጸዋል፡፡
በትምህርት ቤቱ እየተተገበረ የሚገኘው የከተማ ግብርና ስራ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሚማሩትን ትምህርት በተግባር እንዲያዩና እንዲማሩ ብሎም ክህሎት እንዲያሳድግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ይህ ቀደም ብሎ የተጀመረ እና በ90 ቀናት እቅድ ተጠናክሮ የቀጠለ የከተማ ግብርና ስራ ሲሆን ትምህርት ቤቱ አረንጓዴ ፣ ምቹ እና ሳቢ ከማድረግ ባሻገር ለተማሪዎች የግብርና ትምህርትን በተግባር የሚያሳይ ትልቅ የትምህርት መድረክ ሆኖ በማገልገል ላይ እንደሚገኝ ያሳያል።
.