Announcement የመማር ማስተማር ሂደትን በተጠናከረ መንገድ ለመምራት የሱፐርቫይዘሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የመማር ማስተማር ሂደትን በተጠናከረ መንገድ ለመምራት የሱፐርቫይዘሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡

22nd August, 2026

(ነሀሴ 14 /2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ኢንስትራክሽናል ሱፐርቪዥን እና ክሊኒካል ሱፐርቪዥን ላይ ትኩረት ያደረገ የመማር ማስተማር ሂደቱን በተጠናከረ መንገድ መደገፍ የሚያስችል ስልጠና ለ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች እና ለክፍለከተማ ስራ መሪዎች መስጠት ጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በስልጠናው የሚሳተፉ ሱፐርቫይዘሮች የትምህርት ስራውን በንቃት ሱፐርቫይዝ በማድረግ ሂደት ውስጥ የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ስርአት በውጤት የታጀበና ሰላማዊ መማር ማስተማር እንዲኖር ብሎም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስድ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ ጥላዬ አያይዘውም በየጊዜው እየተመዘገበ ያለውን የትምህርት ውጤት በበላይነት የሚመራው የሱፐርቪዥን መዋቅር አካላት ዘመኑ በሚጠብቀው ልክ ራሳቸውን ብቁ የሚያደርጉበትና፤ ቀጣዩ የትምህርት ዘመን በተሳካ መንገድ ለማጠናቀቅ ያላቸው እውቀት ላይ ታካይ የሆነ ግንዛቤ የሚወስዱበት በቀጣይም በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ የሚሆኑ ጉዳዮችን በማንሳት ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮች ለመስራት የሚያስችል መነቃቃት የሚፈጥር ስልጠና መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ አክለውም ሰልጣኞች አላማዉን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ስልጠናው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉና በስራቸው ተግባር ላይ እንዲያውሉት አሳስበዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.