Announcement በከተማ አስተዳደሩ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ተጠናክሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

በከተማ አስተዳደሩ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ተጠናክሮ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

31st July, 2026

(ሀምሌ 23/2018 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደሩ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ተጠናክሮ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እውቀትን በመገንባትና ለቀጣይ የትምህርት ዘመን ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ትልቅ አቅምን እንዲፈጥሩ የሚያግዝ ነው።


የማጠናከሪያ ትምህርቱ ተማሪዎች ከትምህርት ሳይርቁ ቀጣይነት ያለው የጥናት እና የንባብ ልምድ እንዲያዳብሩ የሚያግዝ ሲሆን ለትምህርት ስራው ስኬታማነትና ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የትምህርት ባለድርሻ አካላት የሚናቸውን ሊወጡ ይገባል።


በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርቱ ተጠናክሮ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶችም የ2018 የክረምት በጎ ፍቃድ ማጠናከሪያ ትምህርት በመሰጠት ላይ መሆኑን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

.

Copyright © All rights reserved.