Announcement የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ በክረምት መርሀግብር እየተሰጠ የሚገኘው የማጠናከሪያ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው አስፈላጊውን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ በክረምት መርሀግብር እየተሰጠ የሚገኘው የማጠናከሪያ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው አስፈላጊውን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

06th August, 2026

(ሀምሌ 29/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ ተግባራዊ ያደረገውን የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት አተገባበር መሰረት አድርጎ በሚካሄድ ድጋፍና ክትትል ለሚሳተፉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴ
በክረምት ወቅት የሚሰጠው ማጠናከሪያ ትምህርት ተማሪዎች የመማር ብቃታቸውን አሳድገው በሀገር አቀፉ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መርሀግብር መሆኑን ገልጸው ትምህርቱ በክረምት ወቅት እየተሰጠ እንደመሆኑ ተማሪዎች ትርፍ ጊዜያቸውን አላስፈላጊ ቦታ እንዳያሳልፉ የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል::

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም በድጋፍና ክትትሉ የሚሳተፉ ባለሙያዎች በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት ተማሪዎች በአግባቡ በመማር ላይ መሆናቸውን ክፍል ውስጥ በመግባት ማረጋገጥ እንዲሁም ትምህርቱ ከቢሮ የተላከውን የተጨመቀ ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርጎ በአግባቡ እየተሰጠ መሆኑን በመረጃ ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ቀናሳ በበኩላቸው የማጠናከሪያ ትምህርቱ ከ51ሺ በላይ ለሚሆኑ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች በ63 ክላስተር ማዕከላት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው 1,400 መምህራን በማስተማር ላይ መሆናቸውን ኦረንቴሽኑን በሰጡበት ወቅት አመላክተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.