Announcement በትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት አይነተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ፡፡

በትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት አይነተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ፡፡

03rd November, 2026

በትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት አይነተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ፡፡


(ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2019 ትምህርት ዘመን 3ኛው የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር አፈጻጸምን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክራል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አበራ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር እንደከተማ ትልቅ ትኩረት በመስጠት እየተሰራበት መሆኑን ጠቁመው፤ ይህ ውድድር ትምህርት ቤቶች ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት የምንችልባቸው ቦታዎች እንዲሆኑ ስፖርታዊ ውድድሩና የማለዳ ስፖርት እንቅስቃሴን በማጠናከር ጤናማ ትውልድ ማፍራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አብራርተዋል፡፡


አቶ ተስፋዬ አያይዘውም በውይይቱ ያለፈው አመት የከተማ አቀፍ ስፖርት ውድድር ያለፈበትን ሁኔታ በመገምገም የነበሩ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶችን በማየት ስፖርቱ ቀጣይነቱን ከውጤት ጋር አስጠብቆ እንዲቀጥል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመላክተው፤ የማለዳ ስፖርታዊ እንቅስቃሴም ሙያው ባላቸው አካላት እንዲመራና ከዚህ ጋር ተያይዞ ከወዲሁ በትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮች ተግባራዊ ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.