Announcement የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የሙያ እና የህይወት ክህሎታቸውን አሳድገው ውጤታማ እንዲሆኑ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የሙያ እና የህይወት ክህሎታቸውን አሳድገው ውጤታማ እንዲሆኑ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

15th October, 2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የሙያ እና የህይወት ክህሎታቸውን አሳድገው ውጤታማ እንዲሆኑ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

(ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት አካቶ እና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ያዘጋጀቸውን የሙያ ከህሎት እና የህይወት ክህሎት ማኑዋሎችን የአካል ጉዳተኞች ማህበር ተወካዮችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን፣የልዩ ፍላጎት መምህራን እንዲሁም የክፍለከተማ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት አስገመገመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ አሊ ከማል በመርሀ ግብሩ መክፈቻ በከተማ አስተዳደሩ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሰው ተማሪዎቹ የሙያዊም ሆነ የህይወት ክህሎታቸውን አሳድገው ውጤታማ እንዲሆኑ ቢሮው ሁለቱን ማኑዋሎች ማዘጋጀቱን በመግለጽ በቀጣይ በግምገማው የሚሰጡ የማስተካከያ ሃሳቦችን በማካተት መመሪያዎቹን ወደ ተግባር የማስገባት ስራ የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም ማኑዋሎቹ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በራስ መተማመናቸውን በማሳደግ በማህበረሰብ ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከማስቻላቸው ባሻገር የስራ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና በተግባር ላይ አውለው ህይወታቸውን እንዲያሻሽሉ ታስቦ መዘጋጀታቸውን ጠቁመው ሁሉም ባለድርሻ አካል ለተግባራዊነቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የቢሮው የልዩ ፍላጎት አካቶ እና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በበኩላቸው የመመሪያ ዝግጅቱ በልዩ ክፍል የሚማሩ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ሙያዊ

ሙያዊ ክህሎታቸውን አሳድገው ወደ አካቶ ትምህርት እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን ገልጸው ማኑዋሎቹ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስተባባሪነት የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎችና መምህራንን ጨምሮ የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች በተገኙበት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡


ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የሚሰጠው የክህሎት ስልጠና በዋናነት ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲችሉ ፤ በራስ መተማመናቸውን በማሳደግ በማህበረሰብ ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ፤ የስራ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩና በተግባር ላይ በማዋል እንዲጠቀሙ ብሎም ከሌሎች ጋር ያላቸውን ተግባቦት በማሳደግ የሚዘጋጀው ማንዋል ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የሙያ ክህሎት ስልጠና መስጫ (vocational training and life skill)፤ ለኦቲስቲክ ፤ የአእምሮ እድገት ውስንነት ፤ ዳውን ሲንደረም እና ተደራራቢ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች ስልጠና መስጫነት እንደሚያገለግል ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.