Announcement በከተማ አስተዳደሩ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን ለማላቅ ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል ትምህርት ተቋማት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተጠቆመ።

በከተማ አስተዳደሩ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን ለማላቅ ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል ትምህርት ተቋማት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተጠቆመ።

04th November, 2026

በከተማ አስተዳደሩ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን ለማላቅ ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ የሚጠበቀውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል ትምህርት ተቋማት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተጠቆመ።


(ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን ለማላቅ ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ አተገባበርን መሰረት በማድረግ በትምህርት ተቋማት በተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ዙሪያ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣የስራ አስተባባሪዎችና ሱፐርቫይዘሮች በተገኙበት ውይይት አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ
በከተማ አስተዳደሩ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ውጤትን ለማላቅ የሚያስችል ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰው የ2019 ዓ.ም ትምህርት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ስትራቴጂው በትምህርት ተቋማት ምንያህል ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ በማረጋገጥ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እንዲቻል ድጋፍና ክትትሉ መካሄዱን አመላክተዋል።

ኃላፊው አያይዘውም ርዕሳነ መምህራን ስትራቴጂው የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት በማላቅ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ታስቦ ተግባራዊ መደረጉን በመገንዘብ በድጋፍና ክትትሉ የቀረበውን ግብረ መልስ መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴ በበኩላቸው ስትራቴጂው በሶስት ፕሮግራሞች ማለትም ከትምህርት ሰአት በፊት፣ ከትምህርት ሰአት በኋላ እና ዘወትር ቅዳሜ በክላስተር ደረጃ በሚሰጥ የማጠናከሪያ ትምህርት ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን አስታውሰው ድጋፍና ክትትሉ በየትምህርት ቤቱ ስትራቴጂው ምን ያህል ተግባራዊ እንደሆነ በማየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ መካሄዱን የድጋፍና ክትትሉን ግብረመልስ ባቀረቡበት ወቅት አመላክተዋል።


ስትራቴጂው በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚሰጠውን ትምህርት በመጭመቅ ለትምህርት ቤቶች ማውረዱን ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አበራ ገልጸው ስትራቴጂው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል ለተማሪዎች በቂ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ አስታውቀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.