Announcement የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ በክረምት መርሀግብር እየተሰጠ የሚገኘውን የማጠናከሪያ ትምህርት

የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ በክረምት መርሀግብር እየተሰጠ የሚገኘውን የማጠናከሪያ ትምህርት

14th August, 2026

የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ውጤት ለማላቅ በክረምት መርሀግብር እየተሰጠ የሚገኘውን የማጠናከሪያ ትምህርት መሰረት ያደረገ ምዘና በኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚገኘው ክላስተር ለሚማሩ ተማሪዎች ተሰጠ፡፡


(ነሀሴ 8/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ለማላቅ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘውን የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት መሰረት በማድረግ የአንድ ወር ፈተና መስጠቱን የኮከበ ጽባህ ክላስተር አስታወቀ፡፡

ምዘናው ተማሪዎቹ ለአንድ ወር የተማሩትን ትምህርት ምንያህል እንደተገነዘቡ እና የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርቱን ውጤታማነት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ታስቦ መሰጠቱን የኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርና የክላስተሩ አስተባባሪ አቶ ደለለኝ አስማረ ገልጸው ፕሮግራሙ ተማሪዎችን ለሀገር አቀፉ የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በአግባቡ እንዲዘጋጁ ከማስቻሉ ባሻገር የእረፍት ጊዜያቸውን አላስፈላጊ ቦታ እንዳያሳልፉ ማድረጉን አመላክተዋል።

በየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት የኮከበ ጽባህ 2ኛ ደረጃ ሱፐርቫይዘር አቶ ዮናስ አባተ በበኩላቸው በኮከበ ጽባህ ክላስተር በሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ከሶስት የመንግስት እና ከሁለት የግል ትምህርትቤቶች የተውጣጡ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከሀምሌ 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርቱን በመከታተል ላይ መሆናቸውን ጠቁመው የክፍለከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ፕሮግራሙ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅበትን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.