በትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በአካላቸው ብቁና በአእምሮአቸው ንቁ ዜጋን ለመፍጠት እንደሚያስችሉ ተመላከተ፡፡
(ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ ጤናማና ንቁ ትውልድ ለመፍጠር እንዲቻል ሀሙስ ማለዳ በመካሄድ ላይ የሚገኙ የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡
የካ ክፍለ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በጸሐይ ጮራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የብዙሃን አካል ብቃት እንቅስቃሴ ያካሄደ ሲሆን በመድረኩም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተማሪዎች ጤናማ የሕይወት ዘይቤን እንዲላመዱ እንደሚያስችላቸው ተመላክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የማሕበረሰብ አቀፍ ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር እንግዳወርቅ ዳንኤል ተማሪዎች አካላዊ ብቃታቸውን እንዲያዳብሩ ስፓርት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ጤናማና ንቁ ትውልድ ለመቅረፅ በትምህርት ቤቶች ስፖርት ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

.