(ሀምሌ 18/2018 ዓ.ም) 2018 የትምህርት ዘመን በሁሉም የትምህርት እርከን የመፅሀፍት ጥመርታን 1 ለ 1 ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ለተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ ደብተሮች እና ዩኒፎርሞች በወቅቱ እንዲደርሱ ተደርጋል።
በትምህርት ቤቶች የግብዓት ማሟላት ስራን በተመለከተም የቤተ-መጽሐፍት እና የቤተ-ሙከራ ግብዓቶች የተሟላላቸው የቅድመ አንደኛ ፣ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ድርሻ ከፍተኛ እድገት ያሳየ ሲሆን በተለይም በከተማ አቀፉ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ሀምሳና በላይ ያመጡ ተማሪዎችን ቁጥርን ለማሳደግ ተችላል።
በትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት ፣ የድጋፍ መስጫ ማዕከላትን በማጠናከር ፣ ግብአቶችን በማሟላት ፣ የተማሪዎችን ቁጥር እና የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት ለማሳደግ ተችላል።
መደበኛ ትምህርት ላላገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ትኩረት በመስጠት በተከናወኑ ተግባራት የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርትን ለማጠናከርና የማታ ትምህርትን ለማጎልበት ተችላል።
በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ በትምህርት ዘርፍ የተከናወኑት ተግባራት የትምህርትን ጥራትና ተደራሽነት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበክተዋል።

.