Announcement ብቃት ያለው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመቅረፅ እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ዘርፍ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው፡፡

ብቃት ያለው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመቅረፅ እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ዘርፍ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው፡፡

22nd September, 2026

ብቃት ያለው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመቅረፅ እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ዘርፍ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ ነው፡፡
 
(መስከረም 12/2019 ዓ.ም) የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ፣ ብቃት ያለውና አገር ተረካቢ ትውልድ ለመቅረፅ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት በማሳየት ላይ ይገኛሉ።
 
የትምህርት መሰረተ ልማትን ለማሻሻል በተጀመረው ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ እና በአዲሱ የትምህርት ስርዓት አተገባበር አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
 
ከቅድመ-መደበኛ ፣ ከ1ኛ ደረጃ እና ከ2ኛ ደረጃ ጀምሮ በራስ መተማመን ያለው፣ ጥራትና ሙሉ አቅም ያለው አዲስ ትውልድ መገንባትን መሰረት በማድረግ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ ለማየት ተችላል።
 
የትምህርት ልማት ስራ ውጤት በሂደት በመታየት ላይ የሚገኝ ሲሆን በተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት የትምህርት ጥራት እየተሻሻለ በመምጣት ላይ የሚገኝ ሲሆን ትክክለኛ አቅም ያላቸው ተማሪዎችም ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚናቸዉን ማበርከት የጀመሩት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡
 
በዚህም በአገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ላይ የተደረገው የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም የተማሪዎችን ውጤትና አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲመጣ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
 
በቀጣይም ተማሪዎች ከዚሁ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በትኩረት መስራት የሚገባ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን የቴክኒክና ሙያ ትምህርቶችንም ጭምር እንዲያስተምሩ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።ይህ የተቀናጀ የትምህርት ስርዓት ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ በፅኑ መሰረት ላይ የቆመና የነገዋን አገር በብቃት መሸከም የሚችል አዲስ ትውልድ ማፍራት እንደሚያስችል ታምኖበታል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከናወነው የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ አማካኝነት በገንዘብና በአይነት በርካታ ሀብት ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ተስብስባል። ይህ ንቅናቄ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የመንግሥት ጥረት ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡና የወላጆች ንቁ ተሳትፎ የታየበት ትልቅ እርምጃ ነው።
 
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማስጠበቅ ስራዎች በዘላቂነት ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆኑ  ወላጆች ለልጆቻቸው ትምህርት ያላቸው ተነሳሽነትና ክትትል መጨመሩ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ትልቅ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።.

Copyright © All rights reserved.