ትምህርት የጋራ እውቀትንና እሴቶችን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያሸጋግር የጋራ ሀገራዊ ራዕይን የሚገነባ ድልድይ ነው።
(ጥቅምት 21/2019 ዓ.ም) ትምህርት የአንድ ትውልድ የእውቀት ምንጭ ብቻ ሳይሆን የሀገር የነገ እድገት መሠረት ነው። ዘላቂ ልማት፣ ሁለንተናዊ እድገትና የተሻለ የወደፊት ሀገራዊ አቅም ያለ ጥራት ያለው ትምህርት ሊገነባ አይችልም። በተለይም ዓለም በፍጥነት ወደ ዲጂታል እውቀትና ቴክኖሎጂ በምትሸጋገርበት በዚህ ዘመን፣ የትምህርት ሥርዓታችን የተማሪዎችን እውቀትና ክህሎት ከማሳደግ ባለፈ ለሀገር ልማት የሚያስፈልጉ ብቁ፣ ፈጣሪና ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎችን ማፍራት ይጠበቃል።
ትምህርት የጋራ እውቀትንና እሴቶችን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያሸጋግር፣ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ እና የጋራ ሀገራዊ ራዕይን የሚገነባ ድልድይ ነው። ስለሆነም ትምህርትን በሀገራዊ ልማት ሂደት ውስጥ እንደ ቁልፍ መሣሪያ በመውሰድ፣ በእውቀት፣ በክህሎት፣ በሥነ-ምግባርና በሀገር ፍቅር የታነጹ ዜጎችን ማፍራት የዛሬ ትውልድ ዋነኛ ኃላፊነት ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትምህርት ተደራሽነት፣ ጥራት፣ አግባብነትና ፍትሐዊነት ላይ የላቀ ውጤት ለማምጣት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በሁሉም የትምህርት እርከኖች የተማሪዎችን የጾታ ምጥጥን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል፣ ሁሉም ልጆች የመማር ዕድል እንዲያገኙ በመሰራት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ለማሻሻል ብቃትን ያማከለ ሥርዓተ-ትምህርት በመተግበር፣ ተማሪዎች በእውቀት፣ በክህሎት፣ በሥነ-ምግባርና በሀገር ፍቅር የታነጹ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ዜጎች እንዲሆኑ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ::
በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተግባሪዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው የማላቅ ስትራቴጂ አካል የሆነዉና በትምህርት ቤቶች ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ የሚገኘው ተማሪዎች መደበኛዉን የመማር ማስተማር ትምህርት ከመጀመራቸዉ በፊት እርስ በእርስ እንዲተጋገዙ ለማድረግ የተዘረጋው የጥናት ስርዓት (Before class) ለተማሪዎች የእዉቀት መገነባቢያ መድረክ በመሆን ላይ እንደሚገኝ መምህራንና ተማሪዎች ይገልጻሉ፡፡
ትምህርት የዛሬን ትውልድ ብቻ የሚያንጽ ሳይሆን፣ የነገን ኢትዮጵያ የሚገነባ የልማት መሠረት በመሆኑ በ2019 የትምህርት ዘመን ለስኬታማ የመማር መስተማር ስራ የትምህርት ባለድርሻ አካላት የሚናቸዉን ሊወጡ ይገባል።
.