About አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ጨምሮ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑም ሆነ አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።

አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ጨምሮ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑም ሆነ አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።

24th May, 2025

አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ጨምሮ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑም ሆነ አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።

(ግንቦት 15/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት ማሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የተማሪ ወላጅ ህብረት አመራሮች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት ማሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀጸላ ፍቅረማርያም  አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ጨምሮ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑም ሆነ አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ የሚችለው ወላጆች የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በአግባባቡ መወጣት ሲችሉ መሆኑን በመገንዘብ ቢሮው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል። 

የቢሮው የግንባታ ክትትል ቡድን መሪ አቶ ሙሉነህ ተክለብርሀን በበኩላቸው ወላጆች በህጻናት አካላዊ፣ማህበራዊም እና ስነልቦናዊ  እድገት ላይ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን  በተማሪዎች ውጤት መሻሻል ላይ የወላጆች ሚና በሚል ርዕስ ያዘጋጁትን ስልጠና በሰጡበት ወቅት ገልጸው ከጨቅላነት ጀምሮ በአግባቡ እንክብካቤ ያገኘ ህጻን ጤናማ ንቁ እና አዳዲስ ነገሮችን በፍጥነት መረዳት ስለሚችል ወላጆች በጉዳዩ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ባለሙያ አቶ አራጋው ዘውዴ  ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ግብአት በማሟላት እና አቅማቸውን በአግባቡ አውጥተው ማሳየት የሚችሉበትን ምቹ የመማሪያ አውድ በመፍጠር በትምህታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ወላጆችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ድጋፍና እንክብካቤ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በሚል ርዕስ በሰጡት ስልጠና አመላክተዋል።

የሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎም ሆነ ውጤታማነት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ ቢሆንም ተማሪዎቹ  በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ወላጆች የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ባለሙያው አቶ ሲሳይ ግርማ በሴት ተማሪዎች የትምህርት ቤት ተሳትፎ የወላጆች ሚና በሚል ርዕስ ስልጠና በሰጡበት ወቅት አስረድተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.