Announcement በ2018 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዘገቡ፡፡

በ2018 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዘገቡ፡፡

29th June, 2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ውጤቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ጥራትን በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ በልዩ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝና ከዚህ አኳያ ባለፉት አመታት በከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የታየውን ውጤት በመመልከት ዘንድሮ በ2018 የትምህርት ዘመን የተመዘገበዉን የላቀ ውጤት በማነጻጸር የትምህርት ማህበረሰቡ በትምህርት ልማት ስራዉ ላይ የተከናወኑ ተግባራት ያስመዘገቡትን ውጤት እንዲያውቅና ለቀጣይ ጉልበት በመሆንና የፉክክር መንፈስን በመፍጠር ሀገር የሚገነባ ትውልድ የመፍጠሩ ስራ ግቡን እንዲመታ ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል::
የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ አንዱ አመላካች የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ውጤት መሆኑን የገለፁት ዶክተር ዘላለም 95.85% ወደ ቀጣዩ የትምህርት ደረጃ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት በማምጣት ማለፋቸውን ተናግረው ለውጤቱ መመዝገብ የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ስራዉ ልዩ ትኩረት መስጠቱ ፣ የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር ተጠናክሮ መቀጠሉ ፣ የሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ተደንፎ በትኩረት መሰራት መቻሉ ፣ የመማሪያና የማስተማሪያ ግብዓቶች መቅረባቸው እንዲሁም ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱ ተጠቃሽ መሆናቸውን አብራርተዋል::
አያይዘውም የዘንድሮው ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አያይዘውም የዘንድሮው ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ያስችላል ብለው ለተማሪዎች ፣ ወላጆች ፣ ለትምህርት ቤቶችና መምህራን እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል::


ተማሪዎች ውጤታችሁን የማስፈንጠሪያዉን በመጫን መመልከት ትችላላችሁ

https://aa.ministry.et/#/result.

Copyright © All rights reserved.