Announcement በ2018 በተካሄደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች ዛሬ እውቅናና ሽልማት ስንሰጥ፣ ታላቅ ደስታና ኩራት ይሰማናል።

በ2018 በተካሄደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች ዛሬ እውቅናና ሽልማት ስንሰጥ፣ ታላቅ ደስታና ኩራት ይሰማናል።

05th October, 2026

በ2018 በተካሄደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች ዛሬ እውቅናና ሽልማት ስንሰጥ፣ ታላቅ ደስታና ኩራት ይሰማናል።

ይህ ሥነ-ሥርዓት የውጤታችሁን ዋጋ እዉቅና ለመስጠት ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች ተማሪዎች ተስፋና መነሳሳት የሆናችሁበትን ሚና ለማጉላትም ነው።

ውጤት በአጋጣሚ አይገኝም ፤ከግልጽ ዓላማ፣ ከትጋት፣ ጊዜን በአግባቡ ከመጠቀምና በጽናት ከመቀጠል የሚመነጭ ነው። ዛሬ ያስመዘገባችሁት ስኬት የእነዚህ ጥረቶች ፍሬ ነው ስለዚህ ይህ ክብር ለእናንተ ብቻ ሳይሆን፣ ለቤተሰቦቻችሁ፣ለመምህራኖቻችሁና ለመላው የትምህርት ማኅበረሰብ የሚገባ ነው።

ነገር ግን ይህ ውጤት መድረሻ ሳይሆን የቀጣዩ ስኬት መነሻ ነው። ከዚህ በኋላ የሚጠብቃችሁ የበለጠ ዕውቀት፣ ኃላፊነትና ትልቅ ዓላማ ነው። ዛሬ ያሳያችሁትን ትጋት በማስቀጠል፣ ለራሳችሁ፣ ለማኅበረሰባችሁና ለሀገራችሁ የሚጠቅም ትውልድ እንድትሆኑ አደራ እላለሁ።

የከተማችን የ12ኛ ክፍል ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል። ይህ ስኬት ለትምህርት ዘርፍ በሰጠነው ትኩረት፣ እንዲሁም በተማሪዎች፣ በመምህራን፣ በወላጆችና በአመራሩ የተቀናጀ ጥረት የተገኘ ነው። ለዚህ ሁሉ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ውጤቱ ጥሩ ቢሆንም ከግቡ ገና አልደረስንም ። የትምህርት ጥራትን የበለጠ ለማሻሻልና ለተማሪዎቻችን የተሻለ ዕድል ለመፍጠር በትብብር መሥራታችንን እንቀጥላለን።

ውድ ተማሪዎቻችን፣

የዛሬ ስኬታችሁን ወደ ነገ አስተዋጽኦ ቀይሩት፤ ዕውቀታችሁን ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ጥቅም አውሉት። የምትማሩት ለፈተና ብቻ አይደለም ለሀገር ግንባታ፣ ለማኅበረሰብ ለውጥና ለተሻለ ነገ ነው።

ዛሬ በሽልማት የቆማችሁበት መድረክ ነገ በኃላፊነት፣ በአገልግሎትና በታላቅ አስተዋጽኦ የምትቆሙበት መድረክ ይሁን።
ሕልማችሁን አሳኩ፤ ችግር ሲመጣ አትደክሙ፤ የተሰጣችሁን ዕድል በትጋትና በታማኝነት ተጠቀሙበት። የእናንተ ስኬት የቤተሰቦቻችሁ ደስታ፣ የከተማችን ኩራትና የሀገራችን ተስፋ ነውና።

እንደገና ለሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ !
የዛሬ ስኬታችሁ የነገ ታላቅ አስተዋጽኦአችሁ መሠረት ይሁን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

.

Copyright © All rights reserved.