በገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃቸዉን የጠበቄ ሁለት ባለ 4 ወለል ህንጻዎች ተጠናቀው ለመማር ማስተማር ስራ ዝግጁ መሆናቸው ተገልጻል፡፡
(ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ትምህር ቢሮ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስገነባቸው ሁለት ባለ 4 ወለል ህንጻዎች ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ መሆናቸው ተገልጻል::
ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ የሆኑት ሁለት ህንፃዎች ውስጥ ሁለገብ ህንፃው የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ፣ ዘመናዊ ኩሽና ፣ ወርክሾፖች ፣ ቤተ ሙከራዎች ፣ አዳራሽ ፣ ቤተመፃሕፍት ፣ መፀዳጃና መታጠቢያ ቤት ያካተተ ሲሆን በሁለተኛው ህንፃ በአንድ ክፍል አራት ተማሪዎች መያዝ የሚችል ቁምሳጥን የተገጠመለት ማደሪያ ክፍልና በየወለሉ መፀዳጃና ሻወር ቤት ያለው 300 ተማሪዎች የሚይዝ ህንፃ የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ የሚያደርግ ግንባታ መጠናቀቁ ተገልፃል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ግንባታ ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ ኢንጂነር ሙሉነህ ተክለብርሀን በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲገነቡና የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ እንዲያደርጉ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት መድቦ እያሰራ መሆኑን ገልፀው ቢሮው ህንፃዎቹ ጥራትና አስፈላጊ ክፍሎችን አካተው እንዲሰሩ ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን አብራርተዋል::'
አያይዘውም ቢሮው በየጊዜው ደረጃቸውን የጠበቁና ለተማሪዎች ተገቢና ምቹ አገልግሎት የሚሰጡ ህንፃዎች ሲያስገነባ መቆየቱን አስታውሰው በዚህ ዘርፍ እያከናወናቸው ካሉ ስራዎች ውስጥ በዚህ የትምህርት ዘመን ብቻ 17 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች እያንዳንዳቸው ከ 4 በላይ ህንፃ ያካተቱ ግንባታዎች ተጠናቀው ወደሥራ እየገቡ መሆኑን ተናግረዋል ::
.