የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በተማሪዎች ውጤት መሻሻል ላይ ተጨባጭ ስኬት እያስመዘገበ ይገኛል።
(ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ የሚገኘው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም የተማሪዎችን አካላዊና አእምሯዊ ዕድገት ከመደገፉም በላይ በሁለንተናዊ የትምህርት አቀባበላቸው ላይ ተጨባጭ ውጤት በማምጣት ላይ ይገኛል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የገላን ጉራ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ፋሲል ካባው በትምህርት ቤቱ ከ2,340 በላይ ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው ከዚህ ቀደም በርካታ ወላጆች ለልጆቻቸው የዕለት ምግብ ለማሟላት ይቸገሩ እንደነበር ጠቁመው ይህም ተማሪዎች በምግብ ዕጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡና በውጤታቸውም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮ እንደነበር አብራርተዋል።
አክለውም የምገባ ፕሮግራሙ ከተጀመረ ወዲህ የተማሪዎች የክፍል ተሳትፎ ፣ የትምህርት አቀባበል ፣ የስነ-ምግባር ሁኔታ እና የትምህርት መጠነ ማቋረጥ በከፍተኛ ደረጃ መሻሻሉን በመጥቀስ በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤቱ የሚማሩ የ6ኛ እና የ8 ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ያስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት የፕሮግራሙ መተግበር ካመጣቸው ውጤቶች መካከል መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፕሮግራሙ ለተማሪ ወላጆች የስራ እድልም በመፍጠር ና የወላጆችን ኢኮኖሚያዊ ጫና በማቃለል ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
.