Announcement በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ግብአት አቅርቦቶችና የተማሪዎች ምገባ መርሀ ግብር በትምህርት ጥራት መረጋገጥ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመዘገብ ማስቻላቸው ተጠቆመ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ግብአት አቅርቦቶችና የተማሪዎች ምገባ መርሀ ግብር በትምህርት ጥራት መረጋገጥ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመዘገብ ማስቻላቸው ተጠቆመ፡፡

28th October, 2026

በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የትምህርት ግብአት አቅርቦቶችና የተማሪዎች ምገባ መርሀ ግብር በትምህርት ጥራት መረጋገጥ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመዘገብ ማስቻላቸው ተጠቆመ፡፡


(ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት በ2019 ትምህርት ዘመን በግብአት አቅርቦትና ስርጭት እንዲሁም በተማሪዎች ምገባ ዙሪያ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን ገልጻል::


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ አማካሪና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ስራ ላይ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ በጀት መድቦ እያካሄደ የሚገኘው የተማሪዎች የትምህርት ግብአት አቅርቦትና ምገባ ስራ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ቢሮ ለስራው ስኬታማነትም ተከታታይነት ያለው ምልከታ ፣ ግምገማ እንዲሁም ድጋፍና ክትትል ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው የትምህርት ግብዓት አቅርቦትና የተማሪዎች ምገባ በትምህርት ጥራት ላይ እያመጣ ያለው ለውጥ ከፍተኛና በግልጽ የሚታይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ይህንን ስራ የሚያስፈጽሙ የትምህርት አመራሮች የታለመለትን አላማ እንዲያሳከ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡


የትምህርት ግብአት ፍላጎት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምስራቅ ብርሀነመስቀል በበኩላቸው ባለሙያዎች ለስራዉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና በየጊዜው ድጋፍና ክትትል በማድረግ በሃላፊነት ስሜት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.