Announcement አሁን የሚደረግ ማንኛውም አስተማማኝ የትምህርት ኢንቨስትመንት የነገዋን ብቁና ተወዳዳሪ ኢትዮጵያን የመገንባት መሰረት ነው።

አሁን የሚደረግ ማንኛውም አስተማማኝ የትምህርት ኢንቨስትመንት የነገዋን ብቁና ተወዳዳሪ ኢትዮጵያን የመገንባት መሰረት ነው።

18th September, 2026


(መስከረም 8/2019 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ትምህርት የአንድ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት ከመሆኑም ባሻገር በትምህርት ዘርፍ የሚከናወኑ የትምህርት ልማት ስራዎች ውጤት የሚታየው በነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማላቅ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ነድፎ በትኩረት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የትምህርት ስራ በተማሪዎች አዕምሮ ላይ ሳይታክቱ መስራትን የሚጠይቅ በመሆኑ በተማሪዎች የትምህርት አቀባበልና የትምህርት አሰጣጥ ላይ ከመቼዉም ጊዜ በላቀ ደረጃ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራት ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም ትምህርት የቤት ፣ የአካባቢና የትምህርት ቤት ጥምር ውጤት በመሆኑ።

የወላጅ እና መምህራን ሕብረት ካልተጠናከረ፣ ወላጆች የተማሪዎችን የቤት ሥራና ክትትል ካላደረጉ እና ማህበረሰቡ ትምህርት ቤቶችን የራሱ አድርጎ በሀብትና በክትትል ካልደገፈ የትምህርት ጥራትን በሙሉ አቅም ማረጋገጥ አይቻልም።

የመምህራን የሙያ ማሻሻያ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና የትምህርት ዝግጅት ጥራት በቀጥታ ከተማሪዎች ስኬት ጋር የተያያዘ ነው። የትምህርት ቤቶች ደረጃ፣ የቤተ-ሙከራዎችና ቤተ-መጻሕፍት መሟላት፣ የመማሪያ መጻሕፍት ከተማሪዎች ቁጥር ጋር ያለው ተመጣጣኝነት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅርቦት ለጥራት ወሳኝ ናቸው።

የትምህርት አመራሮች በሙያ ብቃትና በትምህርት አስተዳደር የበሰሉ መሆናቸው፣ አሰራርን ግልጽና ተጠያቂነት ያለው ማድረግ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

በ2019 የትምህርት ዘመን ከተማሪዎች የደብተርና የዩኒፎርም ዝግጅት ባሻገር የጠቅላላ ትምህርት ሥርዓታችን የጥራት ዝግጅት የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የወላጆች፣ የመምህራን፣ የባለሀብቶችና አጠቃላይ የማህበረሰቡ የጋራ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል። 

.

Copyright © All rights reserved.