About የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በትምህርት ተቋማት በተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ ተወያዩ።

የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በትምህርት ተቋማት በተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ ተወያዩ።

17th May, 2025

የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በትምህርት ተቋማት በተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ ተወያዩ።

(ግንቦት 8/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ በቢሮ በሚገኙ ስራ ክፍሎች፣በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንዲሁም በሁሉም የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን  መርሀ ግብሩ በዋናነት የተቋማቱን የ3ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም መሰረት አድርጎ ነው ነው የተካሄደው።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የድጋፍና ክትትሉን ግብረ መልስ አቅርበው በስትራቴጂክ ካውንስል አባላቱ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ድጋፍና ክትትሉ በ3ኛ ሩብ አመት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ እንደመካሄዱ ተቋማቱ በግብረ መልሱ የተሰጡ የማስተካከያ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ በቀሪ የትግበራ ጊዜያት ውጤታማ ማድረግ እንዲችሉ የስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

.

Copyright © All rights reserved.