(ነሀሴ 14/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጀነራል ካውንስል የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሳምሶን መለሰ ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት ቢሮው ጥራት ያለው አጠቃላይ ትምህርትን ለከተማዋ ነዋሪ በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ በከተማው ውስጥ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት በማስፋፋት ውጤታማ ዜጋን ለማፍራትና የመማርና ማስተማር ሂደትን በበላይነት በመምራት ለህብረተሰቡ ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መሆኑን ገልጸው በ2018 ትምህርት ዘመን በተሰሩ ስራዎች የጠቅላላ ካውንስሉ አፈጻጸም እጅ ከፍተኛ መሆኑ አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም በዝግጅት ምእራፍ የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት በ15 ቀናት ያከናወናቸው ስራዎች ላይ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል በለቀጣይ ትምህርት ስራ ምቹ መደላድል መፍጠርና ስራን በእቅድ መሰረት ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የቢሮው የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ከት/ቤት መሻሻል እና ከግንባታ ክትትልና ድጋፍ አንጻር በ15 ቀናት ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራባቸውን ስራዎች እና የመጣውን ለውጥ የሚሳይ ሪፖርት የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቀጸላ ፍቅረማርያም ያቀረቡ ሲሆን በዝግጅት ምእራፍ ዳይሬክቶሬቱ ለዋና ስራ መነሻ የሚሆኑ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬትን የ15 ቀናት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ስራ ክፍሉ በ2019 የትምህርት ዘመን በቂ ዝግጅት በማድረግ ስራዎችን ማከናወን መጀመሩን የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመው ዳይሬክቶሬቱ በ15 ቀናት ውስጥ ያከናወናቸውን ጠንካራ አፈጻጸሞች አጠናክሮ በማስቀጠልና በሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
.