(ሀምሌ 28/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የትምህርት አመራሮች ፣ ባለሙያዎችና መምህራን የተሳተፉበት የክረምት በጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሄዳል፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሌሊሰቱ ተስፋዩ ጽ/ቤቱ በክረምት ወቅት እቅድ ውስጥ አካቶ ከሚሰራቸዉ ተግባራት መካከል አንዱ በክረምት በጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሀ ግብሩ መሆኑን ጠቁመው በመርሀ ግብሩ ላይ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉ መደረጉን እንዲሁም ደም መለገስ ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቁመው ደም የለገሱ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽዎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
.