Announcement 38ኛውን የአለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ በትምህርት ተቋማት ሲካሄድ የቆየው ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕይ በቦሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቀቀ።

38ኛውን የአለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ በትምህርት ተቋማት ሲካሄድ የቆየው ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕይ በቦሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቀቀ።

11th October, 2025

በማጠቃለያ አውደ ርዕዩ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር እንደገና አበበን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ እና የትምህርት ቤቱ አመራሮች እንዲሁም መምህራን እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

የኢፌድሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር እንደገና አበበ በማጠቃለያ አውደ ርዕዩ ባስተላለፉት መልዕክት ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕዩ  ተማሪዎች በሀገራቸው የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን አውቀው ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተዋወቅ እንዲችሉ ታስቦ ከቱሪዝም ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው ተማሪዎች  የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎቹ የት እንደሚገኙ እና ለሀገሪቱ እያበረከቱ የሚገኘው ፋይዳ ምን እንደሆነ እንዲገነዘቡ በማሰብ ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕዩ ቀደም ሲል በዳግማዊ ሚኒሊክ፣በጥቁር አንበሳ እና በጄነራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች  ለእይታ ቀርቦ በዛሬው እለት በቦሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መጠናቀቁን ገልጸው ቢሮው በቀጣይ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ተማሪዎች የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎቹን የሚጎበኙበት እድል የሚመቻች መሆኑን አመላክተዋል።

በአውደ ርዕዩ  እድሳት የተደረገላቸው ታሪካዊ የቱሪዝም ስፍራዎች ፣አዳዲስ መዳረሻዎች እና በዩኔስኮ የተመዘገቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለተመልካች ለዕይታ ቀርበዋል።

.

Copyright © All rights reserved.