Announcement 38ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከፈተ፡፡

38ኛውን የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ ተንቀሳቃሽ ኤግዚቢሽን በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከፈተ፡፡

26th September, 2025

(መስከረም 15/2018 ዓ.ም) በኤግዚቢሽኑ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ሰላማዊት ካሳ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መኔጅመንት አባላት ፣ ተማሪዎች ፣ መምህራንና ርዕሳነ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡

በመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒሰትር  ክብርት ሰላማዊት ካሳ አንደገለጹት የዛሬ ተማሪዎች የነገ በሁሉም መስክ ሀገራቸውን የሚያገለግሎ ዜጎች በመሆናቸው ስለ ሀገራቸው የባህል፣ የታሪክ፣ ተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብቶች እንዲያውቁ እና ሀገሩን የሚውድ ትውልድ ለመፍጠር ተንቀሳቀሽ አውደ ርዕይ እንደተዘጋጀ አንስተዋል።

ዛሬ በይፋ በዳግሜዊ ሚኒሊክ ት/ቤት ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ ለጉብኝት ያቀረብናቸው እና በቀጣዩ ሳምንታትም በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ተ/ቤት፣ በጄ.ታደሰ ብሩ ት/ቤት በመጨረሻም በቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለእይታ የሚቀርቡት  ጠቁመዋል።

ኤግዚቢሽን መዘጋጀት በመዝሙራችን የምንዘምረውን የሚዳስሱና የማይዳሰሱ የኢትዮጵያን የቱሪዝም መስህቦች እና ሀብቶች ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፤ የአገር ውስጥ ቱሪዝምን፤ የባህል ቅርስ፣ ግንዛቤ መፍጠር አንደሆነ  አብራርተዋል። ይህ ዝግጅት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በአዲስ አበባ ት/ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ጋር አንደተዘጋጀ ገልጸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.