ኢትዮጵያ በ2030 ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የትምህርት ስርዓቱን ለማዘመን የያዘችውን እቅድ ከግብ ለማድረስ የመምህራንን ዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ማዳበር ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ፡፡
(ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት በትምህርት ቤቶች ለመተግበር በእቅድ የተያዘውን የዲጂታላይዜሽን እውቀት ውጤታማ ማድረግ ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ ኢትዮጵያ በ2030 ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የትምህርት ስርዓቱን ለማዘመን የያዘችውን እቅድ ከግብ ለማድረስ የመምህራንን ዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ማዳበር ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
የመምህራንን ዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ማዳበር የመማር ማስተማሩን ስራ ቀልጣፋ በማድረግና የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ረገድ ሚና ያለው በመሆኑ መምህራን ዲጂታል ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅማቸውን በማሳደግ ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች በቂ እውቀት ማስተላለፍ እንዲችሉ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
.