Announcement 2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ቅድመ ዝግጅ

2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ቅድመ ዝግጅ

28th June, 2024

2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባን ኦንላይን ለማከናወን እንዲቻል የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተገለጸ።

(ሰኔ 19/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ለክፍለከተማ የቴክኖሎጂና መረጃ ቡድን መሪዎች በ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ተማሪዎችን ኦንላይን በመመዝገብ  መረጃቸውን በአግባቡ ማደራጀት መሆኑን ገልጸው ተቋማቱ ወደ ሲስተም ገብተው የ2017 ዓ.ም ተማሪዎችን ኦንላይን የመመዝገቡ ስራ ውጤታማ እንዲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎች ከወዲሁ መረጃዎችን በአግባቡ የማጠናከር ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በበኩላቸው ስልጠናው ለ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ የሚያግዘውን የትምህርት ቤት መረጃ አስተዳደር ሲስተምን (school information management system) በማስተዋወቅ ምዝገባውን ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን ጠቁመው በቀጣይ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ወደ ሲስተም በማስገባት በሚዘጋጀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተማሪዎችን ኦን ላይን የመመዝገብ ተግባር እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ 

 መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! 

What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D

flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728

TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com     

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/


.

Copyright © All rights reserved.