11ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ ተጠናቀቀ።
(ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በአራዳ ፓርክ "በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር" በሚል መሪ ቃል በድምቀት ያካሄደው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይ ተጠናቀቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀግብሩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ የፈጠራ አውደ ርዕይ ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለተመልካች አቅርበው ዕውቅና እንዲያገኙ ከማስቻሉ ባሻገር ሌሎች ልምድ ቀስመው ተመሳሳይ የፈጠራ ስራዎችን መስራት እንዲችሉ ተነሳሽነትን የፈጠረ መርሀግብር መሆኑን አስታውቀዋል።
ኃላፊው አያይዘውም በተማሪዎችና መምህራን የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎች አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ውጤታማ ከማድረግ ባሻገር የሀገሪቱ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እንዲረጋገጥ መሰረት የሚጥል መሆኑን ጠቁመው አውደ ርዕዩ በዚህ መልኩ በድምቀት እንዲካሄድ በየደረጃው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ፈጠራቸውን ለተመልካች ላቀረቡ መምህራንና ተማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።
.