Announcement ከዛምቢያ የመጡ ከፍተኛ የትምህርት ልዑካን ቡድን አባላት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።

ከዛምቢያ የመጡ ከፍተኛ የትምህርት ልዑካን ቡድን አባላት በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የልምድ ልውውጥ አካሄዱ።

07th March, 2026

 የልዑካን ቡድን አባላቱ የካ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደጃዝማች ወንድይራድ ቅድመ አንደኛ ደረጃ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አብዲ ጃርሶ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ባካሄዱት ልምድ ልውውጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴን ጨምሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው እና የቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ልምድ ልውውጡ በዋናነት ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰቶ ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው የቀዳማዊ ልጅነት ፕሮግራም አካል ሆኖ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሆነውን በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴ አተገባበርና ተቋማቱን ትራንስፎርም ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ለማየት ታስቦ መካሄዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴን ገልጸው የልዑካን ቡድን አባላቱ በተጨማሪም የተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ሂደትን ተመልክተው መደነቃቸውንም አስታውቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ሞዴል ለማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት ሀገራቸው ትልቅ ልምድ የምትቀስምበት ተግባር መሆኑን የልዑካን ቡድኑ አባላት በትምህርት ቤቶቹ ተገኝተው ምልከታ ባካሄዱበት ወቅት አመላክተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.