Announcement በየካ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

19th July, 2025

በምረቃ መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሀላፊ ኢንጅነር አያልነሽ ሀብተማርያም፣ በክፍለ ከተማው የተገነቡት የትምህርት መሰረተ ልማቶች የነገውን ሀገር ተረካቢ ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ፣ ንቁና ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በበጀት አመቱ የበርካታ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻልና አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን የመገንባት ስራ ተሰርቷል ያሉት ሀላፊዋ፣ ግንባታው የስፖርት ሜዳዎች እና ቤተ መፅሀፍትን ጨምሮ የመመገቢያ አዳራሾችን ያካተተ ነው ብለዋል። 

ዛሬ የተመረቁ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የመማር ማስተማር ሥራውን በፈረቃ ይከውኑ የነበሩ ትምህርት ቤቶችን ከፈረቃ እንዲወጡ ከማስቻል ባለፈ ለተማሪዎች ጤናማ እና ምቹ የመማሪያ ከባቢን እንደሚፈጥሩ ኢንጂነር አያልነሽ አክለዋል። 

የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ረታ በበኩላቸው፤ የትምህርት መሰረተ ልማቶች የነገውን ትውልድ የሚገነቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.