Announcement የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጁ ሞጁሎች በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጁ ሞጁሎች በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።

05th June, 2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ውጤታማ እንዲሆን የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጃቸው 4 ሞጁሎች ዙሪያ ለመምህራን ፣ ለአስተባባሪዎች እንዲሁም የክላስተር ማዕከላትን ጨምሮ በየደረጃው ለሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ስጥቷል።
ስልጠናው በዋናነት በሞጁሎቹ የተካተቱትን በጫወታ የማስተማር ስነዘዴ አተገባበርን ፣ በየጭብጡ ለሚደራጁ ኮርነሮች የሚያስፈልጉ መርጃ መሳሪያዎች አዘገጃጀትና አጠቃቀም እንዲሁም በእንግሊዘኛ ትምህርት ሲለበስ እና የክላስተር ሱፐርቫይዘሮችና አስተባባሪዎች መምህራን ውጤታማ እንዲሆኑ በምን መልኩ መደገፍ እንደሚገባቸው ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሀይሉ አስታውቀዋል።ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስልጠናው የተሰጠባቸው ሞጁሎች በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መዘጋጀታቸውን እና በቢሮ የሚገኙ አራት ዳይሬክቶሬቶች ማለትም የመምህራን ልማት ፣ የቀዳማይ ልጅነትና ዘርፈ ብዙ እንዲሁም ሁለቱ ስርአተ ትምህርቶችና የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬቶች እንዲገመግሙ መደረጉን አስታውሰው ስልጠናው ከትምህርት ቀናት ውጭ ዘወትር ቅዳሜና እሁድ ለአምስት ቀናት በተግባር ተደግፎ በመሰጠት ላይ መሆኑን አመላክተዋል።

 መርሀግብሩ የአሰልጣኞች ስልጠና እንደመሆኑ የስልጠናው ተሳታፊዎች በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ መምህራን ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት የሚገባቸው መሆኑን አቶ ሀብታሙ አስገንዝበው የክላስተር ሱፐርቫይዘሮች በየማዕከላቸው ለሚገኙ የመንግስትና የግል የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ ስልጠና በመስጠት ሞጁሎቹ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆኑ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።.

Copyright © All rights reserved.