የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም ለማድረግ የተገዙ ግብአቶች ለተቋማቱ ተሰራጩ።
(ሰኔ 2/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ "የትምህርት ግብዓት ለትምህርት ቤቶች ውጤታማ ትራንስፎርሜሽን!" በሚል መሪ ቃል 137 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ግብአቶችን በመግዛት ለተቋማቱ አሰራጨ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ጥላዬ ዘውዴ በመርሀግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ትራንስፎርም ለማድረግ ባከናወናቸው የተለያዩ ተግባራት እስካሁን 115 ያህሉ ትራንስፎርም ማድረጋቸውን በተቋማቱ በተካሄደ ምዘና መረጋገጡን አስታውሰው ትምህርት ቤቶቹ ግብአት ማሟላታቸው በጫወታ የማስተማር ስነ ዘዴን ተግባራዊ አድርገው ሞዴል እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ህጻናቱ ለቀጣይ የትምህርት ዘመናቸው መሰረት የሚይዙበት እንደመሆኑ በዛሬው እለት ግብአት የተሰራጨላቸው ተቋማት ግብአቶቹን ለሚፈለገው አላማ በማዋል ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

.