Announcement የተማሪ ወላጆች በመማር ማስተማር ውጤታማነት ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ::

የተማሪ ወላጆች በመማር ማስተማር ውጤታማነት ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ::

05th June, 2026

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ከየትምህርት ቤቱ ለተውጣጡ የተማሪ ወላጅ ማህበር ሰብሳቢዎች ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የተማሪ ወላጆች በመማር ማስተማር ውጤታማነት ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጻል፡፡የትምህርት ቤት ማሻሻል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀፀላ ፍቅረማርያም ተማሪዎች በትምህርት ውጤታማ  ብሎም ስነምግባር ያላቸው እንዲሆኑ ወላጆች ያላቸው አስተዋፅኦ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ወላጆች በልጆቻቸው ውጤት መሻሻል ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል::ዳይሬክተሩ አያይዘውም ወቅቱ የትምህርት ማገባደጃ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወላጆች ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ማገዝ እና የትምህርት ዘመኑ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ተማሪ ወላጆች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሐሰን ሺፋ
ትምህርት ቤቶች ምቹና ሰላማዊ እንዲሆኑ እንዲሁም ተገቢውን ግብዓት በማሟላት ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ወላጆች ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበው ፤  የተማሪ ወላጅ አደረጃጀት ከትምህርት ቢሮ ጋር በመሆን መማር ማስተማሩ ውጤታማ እንዲሆን ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል::ግንዛቤ ማጨበጫው በስራ ክፍሉ ባለሙያ በሆኑት በአቶ ሳሙኤል አየለ  የተሰጠ ሲሆን  በ11ዱ ክፍለ ከተማሞች የሚገኙ የተማሪ ወላጅ ሰብሳቢዎች ተሳታፊ ሆነዋል::

.

Copyright © All rights reserved.