Announcement የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተማሪ ወላጆች ማህበር የስድስት ወራት ስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ::

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተማሪ ወላጆች ማህበር የስድስት ወራት ስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ::

07th March, 2026

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተማሪ ወላጆች ማህበር የ6 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ እና አዲስ አበባ ተማሪ ወላጅ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ሀሰን ሺፋ እና በክፍለከተማው ሥር ያሉ ትምህርት ቤቶች ወላጅ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በተገኙበት አካሂዷል::

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የክፍለከተማው ትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪ አቶ ሄኖክ አባይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የወላጅ ኮሚቴው ያለው አደረጃጀት ጠንካራ መሆኑን ገልጸው፤ የተማሪ ወላጅ ማህበሩ የወላጆችን ተሳትፎ ማጠናከርና ስራዎች የትምህርት ቢሮን የስራ አቅጣጫና መመሪያ መሰረት አድርገው እንዲሰሩ መማር ማስተማሩን የማገዝ ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡ 

አቶ ሄኖክ አክለውም ተማሪን በትምህርት ውጤታማ ለማድረግ በተለይም የተማሪ ስነምግባርን ለማሻሻል ከወላጅ ጋር ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባ አመላክተው፤ በ6 ወር ስራ ግምገማው ላይ በአግባቡ ተወያይቶ በእቅዱ መሰረት ያልተሰሩትን ቀሪ ሥራዎች በእቅዱ መሰረት ለማከናወን ተግቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል::

በእቅድ ግምገማው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር እና የኢትዮጵያ ተማሪ ወላጆች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሀሠን ሺፋ ተገኝተው የመማር ማስተማር ስራ ግብ እንዲመታ የተማሪ ወላጅ ማህበር ሚና ትልቅ መሆኑን ጠቁመው በሪፖርቱ የተሰሩ ስራዎች ለዚህ ማሳያ ይሆናሉ ብለዋል፡፡ አያይዘውም የአዲስ ከተማ ክፍለከተማ የተማሪ ወላጅ ማህበሩ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል ::

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተማሪ ወላጅ ማህበር ሰብሳቢ አቶ እንዳሻው ሱልጣን የ2ኛ ሩብ አመት ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ማህበሩ በመማር ማስተማር ስራው ላይ ያከናወናቸው ተግባራትና በቀጣይ መሰራት የሚገባቸው አንኳር ስራዎች ላይ ውይይት በማካሄድ ከትምህርት አመራሩ ጋር በቅርበት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡


.

Copyright © All rights reserved.