Announcement በበይነ መረብ (Online) የሚሰጠዉ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በበይነ መረብ (Online) የሚሰጠዉ የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

27th June, 2026

(ሰኔ 15/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 የትምህርት ዘመን በበይነ መረብ የሚሰጠዉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ከዩኒቨርሲቲ ፣ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ፣ ከአድዋ ድል መታሰቢያና ከአብሮህት ቤተ መጻሕፍት ፕሬዝዳንቶችና ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄዳል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በይነ መረብ (Online) ለሚሰጠው የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከመከናወናቸዉ በተጨማሪም መልቀቂያ ፈተናዉን በስኬት ለማጠናቀቅ ፈተናዉ ከሚሰጥባቸው የፈተና መስጫ ጣቢያ ከሆኑ የዩኒቨርሲቲ ፣ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ፣ ከአድዋ ድል መታሰቢያና ከአብሮህት ቤተ መጻሕፍት ተወካዮች ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች በቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ የተሻለ ስራ ለመስራት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸዋል፡፡ ሀላፊው አክለዉም በቀጣይ ከዋናው ፈተና በፊት ለተፈታኝ ተማሪዎች መለማመጃ ፈተናዎችን መስጠት እንዲቻል የፈተና መስጫ ጣቢያዎች በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ላከናውኑ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በይነ መረብ (online) የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት ሀላፊው ተፈታኝ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በመድረኩም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 የትምህርት ዘመን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍ

.

Copyright © All rights reserved.