Announcement በንፋስ ስልክ ላፍቶ የትምህርት ቤቶች የማስ ስፖርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ የትምህርት ቤቶች የማስ ስፖርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

11th October, 2025

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ "ብቁና ንቁ ትውልድ ለመፍጠር እንተጋለን!" በሚል መሪ ሃሳብ የትምህርት ቤቶች የማስ ስፖርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በሲቢስቴ ነጋሲ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተካሄደው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት እና ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በጋራ የተዘጋጀ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና መሰረት እንደመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ ውጤታማነት ልዩ ትኩረት የሰጠ መሆኑን ጠቅሰው የአካል ብቃት እንቅስቃሴውም ተማሪዎች ብቁና ንቁ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የትምህርት ቤቶች የማስ ስፖርት መርሃ ግብር ቀጣይነት ያለውና ሁሌም በየሳምንቱ ማክሰኞና ሀሙስ የሚከናወን መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሳምሶን ለተግባራዊነቱ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ነጋሽ የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ተማሪዎች በአካልና በአዕምሮ ዳብረው በትምህርታቸው ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ሳይቆራረጥ ማክሰኞና ሃሙስ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

.

Copyright © All rights reserved.