Announcement በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

19th July, 2025

በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ትውልድን ለማነፅና በየጊዜው እያደገ የመጣውን የህዝቡን አዳጊ የመልማትና የልማት ፍላጎት ለማሟላት ለነገ አገር ተረካቢ የተማረ ዜጋ ለማፍራት ወሳኝ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል። 

ትምህርት ለአንድ ሀገር ዕድገትና ልማት ላይ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ  መሆኑን ገልፀው  የትምህርት ተቋማት ላይ ከማህበረሰብ ጋር በጋራ በመስራት የላቀ ውጤት ለማምጣት የመንግስት እያደረገ ያለው ሚና የላቀ መሆኑ ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ የሚጠብቅባቸውን የየራሳቸውን ድርሻ ማበርከት ከቻሉን እና መንግስት መደገፍ የሚገባውን ካደረግ በሁሉም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አቶ አብርሃም አንስተዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት ዛሬ ከተማ አስተዳደሩ እያስመረቀ ያለው ፕሮጀክቶች ለትውልድ ትልቅ ሚና እንዳለው አንስተው ድህንነት ማሸነፍ የሚቻለው ትውልድን በትምህርት በማነፅና ተግቶ በመስራት ነው ብለዋል። 

ትምህርት ላይ ኢንቨስትመንት ማድረግ ከምንም በላይ የነገ አገር ተረካቢን መገንባት እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ አበባ አያይዘው ትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ እጅግ ወሳኝ እንደሆነ በመገለጽ ዛሬ ላይ የተመረቀው  ትምህርት ቤት የትምህርት ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ ያለው ሚና የላቀ ነው ብለዋል።

በምረቃው ፕሮግራም ላይ የከተማና ክ/ከተማ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.