ብቁና ንቁ ትውልድ ለማፍራት እንተጋለን! በሚል መሪ ሀሳብ በልደታ ክፍለ ከተማ የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሂዳል፡፡
የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ በከተማ አቀፍ የትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተማሪዎችን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴው ላይ የተሳተፉ የትምህርት ቤቱ መምህራኖች፣ ተማሪዎች ፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና አመራሮችን የልደታ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ክብረዓለም ደምሴ አመስግነዋል።