Announcement በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

19th July, 2025

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ ተገኝተው  ፕሮጀክቶቹን በይፋ ሲያስመርቁ እንደተናገሩት  የተገነቡት ፕሮጀክቶች  በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል። 

አቶ ጥራቱ አክለውም እነዚህ ፕሮጀክቶች የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ ባሻገር ለትውልድ ግንባታ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ አስታውቀዋል። 

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በበኩላቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡአስተዋፅኦ ላደረጉ የተለያዩ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በዛሬው እለት የተመረቁ ፕሮጀክቶችም በክፍለ ከተማው ለሚገኙ ተማሪዎች የተሻለ የመማሪያ አካባቢ በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና እንደሚኖራቸው ገልፀዋ፡፡

በዛሬው እለት በከተማው ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከልም  7 የቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ 3 የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ እና 4 የሁለተኛ ደረጃ በድምሩ 14 አዲስ ት/ቤቶች ግንባታ እንዲሁም በነባር ት/ቤቶች ላይ 38  ከ G+1 እስከ G+4 ህንፃዎችን የያዘ 1655 ተጨማሪ  የመማሪያ ክፍሎች እንዲሁም   ⁠17 የመመገቢያ አዳራሽ፣ 30 መጸዳጃ ቤቶች እና የመጠጥ ውሀ አገልግሎት መስጫ፣ 11 የስፖርት ሜዳዎች፣ 2 የቤተሙከራ ክፍሎች፣ 1 ቤተመጽሐፍት፣ 10 ት/ቤቶች ላይ ምድረ ግቢውን የማስተካከል እና ማስዋብ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በበጀትዓመቱ በድምሩ በትምህርት ሴክተሩ 150 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.