Announcement በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያስበቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶችና የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያስበቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶችና የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

19th July, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል ወይዘሮ ዓለምፀሀይ ሽፈራው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ ትምህርት ቤቶችን መርቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት አርገዋል።

በዛሬው እለት ከተማ አስተዳደሩ በ2017 በጀት አመት ከ5.2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ያስገነባቸውን 150 ትምህርት ቤቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ይሆናሉ ብለዋል  ወይዘሮ ዓለም ፀሀይ ሽፈራው በምረቃው ወቅት ፕሮጀክቶቹ በጥራትና ደረጃቸዉን ጠብቀዉ የተሰሩ  14 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ፤ በ64 ነባር ትምህርት ቤቶች ላይ ማስፋፋያ የተገነቡ 1655 የመማሪያ ክፍሎች ፣ የአይሲቲ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መፅሀፍቶች ፣ የስፖርት ሜዳዎች ፣ ምድረ ግቢዎች ፣ የመጸዳጃ ቤቶች እና የውሃ አገልግሎትን  ጨምሮ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና መምህራን ምቹ የማድረግ ስራዎችን ያካተተ ነዉ ብለዋል ኃላፊዋ፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በትምህርቱ ዘርፍ የሰራቸው ታላላቅ ስራዎች የነገር ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ የሚሰራ ፓርቲ ስለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል ወይዘሮ ዓለምፀሀይ ከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን እንደስሟ አዲስና ለነዋሪዎቿ የምትመች ከተማ ከማድረግ ባሻገር የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናትና ወጣቶች  ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው ያሉት ወይዘሮ ዓለምፀሀይ ባለፈው ሳምንት የተመረቁና ዛሬ የሚመረቁ 150 ትምህርት ቤቶች ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል።

ዛሬ የተመረቁ ትምህርት ቤቶች መሰረታዊ የትምህርት ግብዓቶችን ያሟሉና ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው ያሉት ኃላፊዋ ይህንን እድል በአግባቡ የመጠቀምና ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ የማህበረሰቡ ኃላፊነት መሆኑንም አሳስበዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ በበኩላቸው ብልፅግና  ከሚሰራቸው ታላላቅ ልማቶች ባሻገር የሰው አዕምሮ ልማት ላይ የሚሰራ ፓርቲ መሆኑን ገልፀው ትውልዱ ይህንን እድል እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለሀገር ግንባታና ለሁለንተናዊ ብልፅግና ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።

በክፍለ ከተማችን ውስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶች ፍሬ እያፈሩ ነው። ይህ የከተማ አስተዳደሩ ጥረትና ሀብት ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህንን መጠበቅና መንከባከብ  የማህበረሰቡ ኃላፊነት መሆን እንዳለበትም ገልፀዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ፣ የከተማ አስተዳደሩ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ አይሻ መሐመድ ፣የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.