Home የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሆኑ ህፃናት ሁለንተናዊ ዕድገት ለማለረጋገጥ በሙሉ አቅሟ እየሰራች ያለች ከተማ፤ አዲስ አበባ!

የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሆኑ ህፃናት ሁለንተናዊ ዕድገት ለማለረጋገጥ በሙሉ አቅሟ እየሰራች ያለች ከተማ፤ አዲስ አበባ!

20th December, 2025

ከለውጡ በፊት በሀገራችን  ያልነበረዉ የቅድመ-ልጅነት እድገት እና እንክብካቤ፣ ከለዉጡ ማግስት፥ የነገ ሃገር ተረካቢ ለሆኑ ህፃናት፣ የነገ ዕድገታቸው ዕዳ የሌለበት እና ለትውልድ የሚተርፍ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎች በትኩረት እየሰራ የሚገኘው  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማት፣ ሁሉን አካታች እንዲሆን ለሀገር እና ለትውልድ የሚበጀውን ሁሉ በማቀድ ቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም  በመንደፍ እና ወደ ተግባር በመቀየር አዳዲስ ለዉጦችን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

ይህ ፕሮግራም  ልጆቻቸውን በህፃናት ማቆያ ከፍለው ማቆየት የማይችሉ ቤተሰቦች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፣ ወጪው ሙሉ በሙሉ  በመንግስት እየተሰራበት የሚገኝ ነዉ፡፡

አነስተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰብ የተገኙ ዕድሚያቸው ከ 3 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የቀጥታ አልሚ ምግብ በየወሩ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር ለከፍተኛ  ችግር ተጋላጭ  የሆኑ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ድጋፍ  እየተደረገላቸውም  ይገኛል፡፡

በቀዳማይ  ልጅነት ፕሮግራም የሚሰራዉ ስራ ህፃናት በትምህርታቸው የተሻሉ፤ በስነምግባር የታነፁ እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለዉ በመሆሩ በትኩረት እየተሰራበት የሚገኝ ሌላዉ ሰዉ ተኮር የልማት ስራ ዉጤት ነዉ፡፡ 

ሃገርና ትዉልድን ለመታደግ ቀን ከሌት እየታተረች ያለችዉ ከተማ አዲስ አበባ፣ በቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ብቻ ሳትወሰን በሌሎች ሰዉ ተኮር የልማት ስራዎቿ የተያያዘችዉን የብልፅግና ጉዞ የበለጠ እንዲረጋገጥ አበክራ የምትሰራ ይሆናል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.