Announcement በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በእንጦጦ አንባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በእንጦጦ አንባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።

11th October, 2025

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች የማለዳ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሀግብር በእንጦጦ አምባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት "ብቁ እና ንቁ ትውልድ ለመፍጠር እንተጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ ተካሂዷል፡፡  

በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ፤ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሳሙዔል ተገኝ የትምህርት ቤቱ መምህራን፣ አመራሮችና ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሃግብሩ  ላይ ተገኝተው  ባስተላለፉት  መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በሁሉም ደረጃ ያሉ ተማሪዎች በአካዳሚክ እውቀታቸው የበቁ እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን በአካል ብቃታቸው የበቁ እና ጤንነታቸው የተጠበቀ የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ምቹ የስፖርት ሜዳ እንዲኖር በማድረግ የትምህርት ሰዓት በማይነካ በሳምንት 2 ቀናት የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተግባራዊ እንዲደረግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው በመግለጽ በቀጣይም በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ አሳስበዋል፡፡

በመርሀግብሩ የተገኙ እንግዶችና ተማሪዎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴው የተሳተፉ ሲሆን የስፓርት እንቅስቃሴው በሳምንት  2 ጊዜ ጠዋት ጠዋት ማክሰኞና  ሐሙስ በሁሉም በትምህርት ቤቶች በቋሚነት የሚካሄድ መሆኑና በትምህርትና በወጣቶችና ስፖርት ቢሮዎች መካከል በጋራ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.