ከሀይማኖት አባቶች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የጤና ባለሞያዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም ከተለያዩ የሙያ ማህበረሰቦች ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ጠረኗ እና መልኳ ተቀይሮ ባማረችውና ውበት በተጎናጸፈችው አዲስ አበባ በግንፍሌ ወንዝ ዳርቻ ችግኝ ተክለናል።
በሁሉም የከተማችን አካባቢዎች በተዘጋጁ 271 ቦታዎች መላው የከተማችን ነዋሪዎች በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት በነቂስ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። ማለዳ ላይ በጀመርነው መንፈስ ቀጥለን በእቅድ የያዝነዉን ግብ እንደምናሳካ እርግጠኛ ነኝ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
.