Resource የስራ ክፍሎች ወርሀዊ እቅድ አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ በዘርፍ የሚደረገው ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

የስራ ክፍሎች ወርሀዊ እቅድ አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ በዘርፍ የሚደረገው ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

15th March, 2025

የስራ ክፍሎች ወርሀዊ እቅድ አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ በዘርፍ የሚደረገው ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

(መጋቢት 5/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት፣የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት፣ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር እንዲሁም የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ዳይሬክቶሬቶች የየካቲት ወር እቅድ አፈጻጸም  ግምገማ እና በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ዲናኦል ጫላ በሁለቱ ስርአተ ትምህርቶች እንዲሁም በሬዲዮ ትምህርትና በፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች በየካቲት ወር የተለያዩ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና በሂደት የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንዲቻል ውይይቱ መካሄዱን አመላክተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.