Announcement ትውልድን መቅረጽና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የጋራ ኃላፊነት ነው።

ትውልድን መቅረጽና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የጋራ ኃላፊነት ነው።

14th September, 2026



(መስከረም 4/2019 ዓ.ም) አዲሱ የ2019 የትምህርት ዘመን ሲበሰር፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱና ወላጆች ለልጆቻቸው የተሻለ ነገን ተስፋ አድርገው ደፋ ቀና ሲሉ መመልከት በራሱ ታላቅ አገራዊ ጸጋ ነው።


ትምህርት የሰውን ልጅ ስብዕና ዳግም የሚገነባ ረቂቅ መሣሪያ ከመሆኑም በላይ ፣ በሁለንተናዊ አስተሳሰብ ትርክት ግንባታ ውስጥ አገርን በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም የማዕዘን ድንጋይ ነው።


ይህ የትምህርት መጀመሪያ ወቅት የክፍል በሮች የሚከፈቱበት ብቻ ሳይሆን አዲስ የተስፋና የዕውቀት በር ወለል ብሎ የሚከፈትበት ሊሆን ይገባል።


ይሁንና ይህን ተስፋ ወደ እውነታ ለመቀየር፣ የትምህርት ጥራትን እንደ ሀገራዊ ደኅንነት ጉዳይ ቆጥሮ ይበልጥ መሥራትን የግድ ይላል።


የ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን አገራዊ ብዝሃነትን በአዲስ መልክ ወደሚተረጉም፣ ዜጎችን በጋራ ጥቅሞች ዙሪያ ወደሚያስተሳስር እውነተኛ የአገረ መንግሥት ግንባታ ማዕከልነት የሚያሸጋግር ሊሆን ይገባል።


አገር የሚገነባው በአብዛኛው ማኅበረሰብ ዘንድ የጋራ ስምምነት በተደረገባቸው አዎንታዊ ትርክቶች እንጂ በከፋፋይ የበቀል ትረካዎች አይደለም።


ይህን ስትራቴጂያዊ የአስተሳሰብ ሽግግር እውን ለማድረግ ደግሞ የትምህርት ጥራት ጉዳይ ቁልፉ መሣሪያ ነው።

.

Copyright © All rights reserved.