Home የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ለመምህራን እየተዘጋጀ በሚገኘው ዲጂታል መታወቂያ ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስራ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ።

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ለመምህራን እየተዘጋጀ በሚገኘው ዲጂታል መታወቂያ ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስራ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ።

22nd November, 2025

ውይይቱ በዋናነት  የመምህራኑን ትክክለኛ መረጃ ወደ ዳታ ቤዝ በአግባቡ ገብቶ መታወቂያው  ታትሞ ለመምህራኑ እንዲሰራጭ የክፍለ ከተማ የስራ አስተባባሪዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የመረጃዎቹን ትክክለኛነት እንዲያረጋግጡ መዘጋጀቱን ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ዲጂታል መታወቂያው መምህራኑ የከተማ አውቶብስን ጨምሮ ለሚጠቀሟቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ከመዋሉ ባሻገር በተለያዩ ህገወጥ አካላት የሚዘጋጁ ፎርጅቱ መታወቂያዎች አገልግሎት ላይ እንዳይውሉ የሚያደርግ በመሆኑ ክፍለ ከተሞች የመምህራኑን ትክክለኛ መረጃ በማጥራት ወደ ዳታ ቤዝ እንዲገባ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም የመምህራኑ ትክክለኛ መረጃ ተጣርቶ ወደ ዳታቤዝ እንደገባ ታትሞ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን የሚሰራጭ መሆኑን ገልጸው ስራ ዳይሬክቶሬቱ ከመምህራን ልማት እና ከአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች ጋር በጋራ በመሆን ስራውን እየተከታተለ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በመርሀግብሩ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና አተገባበር ያለበት ሁኔታ ከመገምገሙ ባሻገር በ2018 ዓ.ም በበይነ መረብ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተከናወኑ የሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተገምግመዋል።


.

Copyright © All rights reserved.