Announcement ከመማር ማስተማር አንፃር፡-

ከመማር ማስተማር አንፃር፡-

13th July, 2026


ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተማሪዎችን ተደራሽነት፣ አካታችነትና የትምህርት ጥራት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል። በዘርፉ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች ፡-

•የተደራሽነት ዕድገት፡- ባለፉት አምስት ዓመታት የተማሪዎች ቁጥር ከ829,158 ወደ 1,334,830 ከፍ ብሏል። በ2018 በጀት ዓመትም ይህንኑ የተማሪዎች ቁጥር በማሳካት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ81,093 ብልጫ ማሳየት ተችሏል።

•የትምህርት ጥራትና ውጤት፡- ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አላፊዎች ከ80.2% ወደ 97%፣ የ8ኛ ክፍል ከ36.1% ወደ 96.2%፣ እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አላፊዎች ከ25.45% ወደ 31% ማደጉን አብራርተዋል።

•የትምህርት ግብዓት አቅርቦት፡- የመፅሐፍና ተማሪ ጥምርታን 1፡1 ማድረስ የተቻለ ሲሆን፤ የደብተርና ዩኒፎርም አቅርቦትም ትምህርት ከመጀመሩ አስቀድሞ በክረምቱ ሙሉ በሙሉ ለተማሪዎች ተደራሽ ሆኗል።

•አካታች ትምህርት፡- የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት 124 ማዕከላት ተደራጅተው 34,117 ተማሪዎች የትምህርት ዕድል አግኝተዋል። ለአይነ ስውራንና ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የብሬል መፃህፍት፣ የድምጽ መሳሪያዎች እና የተለያዩ የአካል ድጋፍ ግብዓቶች ቀርበውላቸዋል።

•የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ፡- ማህበረሰቡን በማስተባበር 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት (በገንዘብ፣ በአይነት፣ በጉልበትና በእውቀት) በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን የመጠገንና ግብዓት የማሟላት ስራ መሰራቱን ከንቲባዋ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

.

Copyright © All rights reserved.