Announcement የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶችና የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው ትምህርት ቤቶችና የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

19th July, 2025

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ  ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሰ ፣ የክ/ከተማው ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ መምህራን እንዲሁም የክ/ከተማው ነዋሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪውን የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመልሱ በርካታ ፕሮጀክቶችን መገንባት መቻሉንና የከተማ አስተዳደሩ  ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት በበጀት ዓመቱ በርካታ በጀት በመመደብ ትምህርት ቤቶችና የአይሲቲና ሌሎች የትምህርት መሰረተ ልማት መገንባት መቻሉንና በዚህም የተማሪ ጥምርታን በመቀነስ ለመማር ማስተማር ምቹ ሁኔታን መፍጠር መቻሉን አንስተው የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ የሰጠው ትኩረት የነገዋን ኢትዮጵያ ተስፋ በፅኑ መሰረት ላይ የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በክፍለ ከተማው ልማትን ባህል በማድረግ በርካታ ትልልቅ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በማህበረሰቡና በባለሀብቱ ተሳትፎ እየተገነባ እንደሚገኝ ጠቅሰው አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ጥራት ፣ ፍትሀዊ ተደራሽነትና ለማረጋገጥ በ2017 በጀት ዓመቱ በርካታ የትምህርት ፕሮጀክቶችን ሰርቶ በማጠናቀቅ ማስመረቅ መቻሉንና አንስተው ህብረተሰብም ሆነ ባለድርሻ አካላት ፕሮጀክቶቹ ጉዳት እንዳይደርስባቸውና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ ሊንከባከባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል ።

.

Copyright © All rights reserved.