Announcement በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ፡፡

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የተገነቡ የትምህርት መሰረተ ልማቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ፡፡

19th July, 2025

በዛሬው እለት በመዲናዋ ከተመረቁ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች መካከል በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የተገነቡ ፕሮጀክቶች የከተማ አስተዳደሩና የክፍለ ከተማ አመራሮች እንዲሁም የትምህርት ዘርፉ ማህበረሰብ በተገኙበት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል::

 በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በመዲናዋ በአጠቃላይ በ5.2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግልሎት ክፍት መደረጋቸውን ገልፀው ትውልድን ለማነፅ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች የጥራት ደረጃቸዉን ጠብቀዉ መገንባታቸውን ገልፀዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው የተመረቁ የመማሪያ መሰረተ ልማቶች የነገውን ትውልድ በመልካም ሁኔታ ላይ ለማስቀመጥ የተገነቡ መሆናቸውን ገልፀው ብቁና ተወዳዳሪ ትውልድ ለመፍጠር ታሳቢ ተደርገው የተገነቡ መሆናቸውን አስታውቀዋል::

በክፍለ ከተማው በዛሬው እለት የተመረቁ ፕሮጀክቶች በወረዳ 14 የሚገኘው ፊውታራሪ ት/ቤት ጂ+4 የመማሪያ ህንፃ፣ ጂ+2 የአስተዳደር ህንፃ፣ ጂ+2 የኬጂ መማሪያ ህንፃ እንዲሁም በአዲስ ፋና ት/ቤት ጂ+4 የመማሪያ ህንፃ ተገንብተው የተመረቁ ሲሆን በወረዳ 12 በሚገኘው ብስራት ት/ቤት የመመገቢያ አዳራሽ እና የማብሰያ ክፍል እንዲሁም በወረዳ 8 በሚገኘው ዳግማዊ ብርሐን ት/ቤት ጂ+4 የመማሪያ ህንፃ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል::

.

Copyright © All rights reserved.