በየደረጃው የሚገኙ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቫይዘሮች የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ ሆኖ የተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር እንዲሻሻል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው ተገለ ጸ።
(ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዝን ዳይሬክቶሬት በዘርፉ የ2018 ዓ.ም የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም እና በትምህርት ተቋማት በተካሄደ የሱፐርቪዥን ግኝት ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ጋር ውይይት አካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ጥላዬ ዘውዴ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በየትምህርት ቤቱ የሚደረግ የሱፐርቪዥን ስራ ውጤታማ የመማር ማስተማር ስርአት ሰፍኖ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል እያበረከተ የሚገኘው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰው በ2018 ዓ.ም በ9 ወር ውስጥ ከቢሮ ጀምሮ በክፍለከተማና ወረዳ በተዋቀሩ ክላስተር ማዕከላት የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ለትምህርት ስርአቱ ውጤታማነት የነበራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ምክትል ቢሮ ኃላፊው በበጀት አመቱ 9 ወራት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አፈጸጸም እና በሱፐርቪዝን ግኝቱ መሰረት ጠንካራ አፈጻጸሞችን በማስቀጠል እና በሂደት የተስተዋሉ እጥረቶችን በመቅረፍ በአመቱ መጨረሻ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዝን ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ቀናሳ በበኩላቸው ስራ ክፍሉ በየደረጃው የሚገኙ የሱፐርቪዝን መዋቅሮችን በማስተባበርና በትምህርት ተቋማት በመገኘት የድጋፍና ክትትል ስራን ጨምሮ የተለያዩ
.